ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።  
 
  reporter 01/22/2025 7:06am (UTC)
   
 
የዘንድሮ የቡሔ አከባበር በአዲስ አበባ

Wednesday, Oct 06th

English Version

የዘንድሮ የቡሔ አከባበር በአዲስ አበባ

E-mail Print PDF
User Rating: / 0
PoorBest 

ጓል - አሸንዳ - ዕንቡጥ ፅጌረዳ
ጓል አሸንዳ
ዕንቡጥ ፅጌረዳ፡፡

ከፈረንጅ ሳትዋስ ሜክ አፕና ፍሪዝ
ጓል አሸንድዬ ውብ ናት የምታፈዝ፡፡

በአልቦና ድሪ በጉትቻ ማርዳ
ደምቃለች ተውባ ጓል አሸንዳ፡፡

ሽር አለች በሜዳ ተሻገረች ገረብ
ጓል አሸንድዬ በባህሏ ልትዋብ፡፡

በጥልፍ የተዋበች ታጣቂዋ አሸንዳ
ቀልብ ሰራቂ ናት ጓል አሸንዳ፡፡

ጓል አሸንዳ
ዕንቡጥ ፅጌረዳ፡፡

ገረብ ተሻጋሪ ሽር ባይ በሜዳ
ንፅሒት ድንግል ናት ጓል አሸንዳ፡፡

ገረብ ተሻጋሪ ሽር ባይ በሜዳ
ባህል አክባሪ ናት ጓል አሸንዳ

ገረብ ተሻጋሪ ሽር ባይ በሜዳ
ጓል አሸንዳ ዕንቡጥ ፅጌረዳ፡፡
(ጓል - ሴት ልጅ፤ ገረብ - ወንዝ)
(ያሲን ዑመር፤ትውፊት፣2001)

* * * * * *

የነሐሴ 16 የአሸንዳ በዓል ግብዓቶች
ልጃገረዶች ለአሸንዳ ቆረጣ ሲሄዱ የሚለብሱት በሕብረ ቀለማትና በአበባ ያጌጠ የሻማ ቀሚስና፣ ኮንጎ ጫማ፣
የአሸንዳ ልጃገረዶችና ጠባቂ እረኞቻቸው ከአሸንዳ ቆረጣ በፊት ለሚያከናውኑት ባህላዊ የመንፃት ሥርዓት ዘለው የሚሻገሩት ወንዝ፣
ባለጃኖ ጥለትና በተለምዶ የራያ ልብስ በመባል የሚታወቀው የሀገር ባህል ቀሚስ (መልጐም)፣ እና ባለ ሕብረቀለም መቀነት (ትፍትፍ)፣
የአሸንዳ ልጃገረዶች የሚቆነጃጁበት ኩል፣ የኩል መደቆሻ ብረት ምጣድና አሎሎ፣
የአሸንዳ ልጃገረዶችና እናቶች ቀጭን ሹሩባ (ጋምአሮ) ሲሰሩ ፀጉራቸው የሚከፈልበት ወስፌ፣
ባህላዊ የራያ ጭስ፣ ለጭሱ መታጠኛነት (መሞቂያነት) የሚያገለግል የሸክላ ምድጃ፣ እና የመሸፋፈኛ በርኖስ፣
በቅርቡ የታጨች ወይም ካለፈው አሸንዳ ወዲህ የተዳረች ሙሽሪት የምትቀመጥበት አጐዛ፣
ባህላዊ የቡና ሥርዓት የሚከናወንበት የትግሬ ሸክላ ጀበና፣ ስኒዎች፣ ባማረ አለላ የተሰፋ የአምባሻ ማቅረቢያ ቆለምሽሽ፣
በዛጐል የተጌጠ የቅቤ መያዣ ቅል፣ እና የአሸንዳ ልጃገረዶች ፀጉራቸውን ካጎፈሩ ጎረምሶች መካከል ሎሚ የሰጣቸውና ቀልባቸውን የሳባቸውን በመምረጥ የሚቀቡት ቅቤ፣
የአሸንዳ ልጃገረዶችን የሚያጅቡ እረኞች የሚይዟቸው ሽመሎች፣ ከጭረት የተሰሩ ወንጭፎች፣ በሸንበቆ የተሰሩ ዋሽንቶች፣ የበግ ለምዶች፣ ለገበጣ መጫወቻነት የሚያገለግሉ ጠጠሮች፣ ለልጃገረዶቹ በስጦታ መልክ የሚቀርቡ ሎሚዎችና የብር ጌጣጌጦች፣ ለአቅመ-አዳም የደረሱ ጎረምሶች ክምክም ጎፈሬያቸው ላይ ሻጥ የሚያደርጓቸው ሚዶዎች፣ ጎረምሶቹ ኮራ ጀነን ብለው ጥርሳቸውን የሚፍቁባቸው ክትክታዎች፣
አሸንዳዬ ጨዋታ ለሚጫወቱ ልጆች በሽልማት መልክ የሚሰጥ አምባሻ፣ ድፎ ዳቦ (ጎጎ)፣ ህብስት (ጓጉባ፣) ጠላ፣ አረቄ፣ ሎሚ፣ ወተት፣ ወዘተ ናቸው፡፡
(ያሲን ዑመር፤ትውፊት፣2001)

* * * * * *

ይድነቃቸው ተሰማ (ከመስከረም 1 ቀን 1914-ነሐሴ 13 ቀን 1979)

ገና የ14 ዓመት አዳጊ ወጣት እያሉ በ1935 ዓ.ም በአገራችን የመጀመሪያው የስፖርት ክለብ የሆነው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ሲቋቋም ለቀሪው ድንቅ የሕይወታቸው ጥሪ መጠሪያ ይሆን ዘንድ ወደዚህ ቡድን ገቡ፡፡ ይህም ድልድይ ሆኗቸው ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለመመረጥ በቁ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ኳስ ዕረፍታቸው፣ ኳስ ሽርሽራቸው፣ ቀጠሯቸው ሁሉ፣ ኳስ ሜዳ ሆነ፡፡ ይድነቃቸው ክለባዊና አገራዊ የድርሻ ምዕራፎቻቸው የሚነበቡት 23 የእግር ኳስ ቡድንና ከ1948 ዓ.ም. እስከ 1954 ለ15 ጊዜያት በተሰለፉበት የብሔራዊ ቡድን ውስጥ ነው፡፡ ነገር ግን ከሌሎች ተለይተው በመውጣት ታላቅ አገራዊና አህጉራዊ የስፖርት ዓለም አስተዋፅኦቸው የሚጀምረው ከእንዲህ ዓይነቱ የኳስ ተጫዋችነታቸው ምዕራፍ በኋላ ነው፡፡
(ሰሎሞን ጥላሁን፣ ደማቆቹ፣ 2000)

* * * * * *

እርሳስ
ይህ ንጥረ ነገር በጣም ልል እና ከባድ በመሆኑ ይታወቃል፡፡ ከመደበኛ ብረታ ብረቶች መሀል በክብደት የሚበልጠው ወርቅ ብቻ ነው፡፡ እርሳስ በጣም ልል ከመሆኑ የተነሳ በቀላሉ በጥፍር ሊቧጨር ይችላል፡፡ ይህ ስጦታው ስላለም እርሳስ ቧንቧዎችን ለመስራት በጣም ተፈላጊ ሆነ፡፡ የጥንት ሮማውያን እርሳስን ለውሃ ማስተላለፊያና የሕዝብ መታጠቢያዎች ማካሄጃ ይጠቀሙበት ነበር፡፡ እርሳስ በጣም ዝቅ ባለ ሙቀት ስለሚቀልጥ ለመበየጃም ይጠቀሙበት እንደነበር ይነገራል፡፡
አሁን ባለንበት ዘመን የአቶሚክ ኃይል አስፈላጊነት እያደገ በመሄዱ እርሳስ ከሰራጺ ጨረር (ራዲዬሽን) እንደ ጋሻ እየሆነ በመከለል ስለሚረዳ ጠቃሚነቱ ታውቆለታል፡፡ ለምሳሌ ሰራፂ ጨረር የሚለቅቁት እንደ ዮራኒዬም ያሉት ንጥረ ነገሮች ጋማ የተባሉ ለሰው ልጅ አደገኛ የሆነ ጨረሮች ይለቅቃሉ፡፡ ታዲያ በእርሳስ ግርዶሽ ተጋርዶ እንደሆነ እነዚህ ጨረሮች ስለሚታገዱ ሰውን ከመጎዳት ይቆጠባሉ፡፡ እርሳስ እንዲሁም በየሆስፒታሎች የሚገኘውን ኤክስሬይ ጨረር ወይም ራጅ ጨረሩ አልፎ በሰውነት ላይ ጉዳት እንዳያደርስ በመጋረድ ይረዱናል፡፡ እርሳስ በተጨማሪም በአንድ ሬዲዮ ጣቢያ ድምጽ ሲቀረፅም ሆነ ሲተላለፍ ፀጥታ እንዲሰፍንና የውጭ ድምጽ እየገባ እንዳያውክ የሚጋርድና የሚረዳም ነው፡፡ ብዙ ጊዜ በአነጋገር በተፈጠረው ስህተት እርሳስ ማለት ለምንጽፍበት እርሳስ ምንጭ አይደለም፡፡ የመጻፊያው እርሳስ ግራፍት ከተባለ ሌላ ንጥረ ነገር የሚሠራ ነው፡፡ የእርሳስ ዋናው ዘመናዊ አገልግሎት በመኪና ባትሪ ሥራ በኩል ነው፡፡
(ሻምበል አፈወርቅ ዮሐንስ፣ ዓለም የሠራተኞች ናት)

* * * * * *

በታታሪነት ከጉንዳን የማይተናነሱት

በታታሪነት ንቦችም ከጉንዳን የሚተናነሱ አይደሉም፡፡ ግማሽ ኪሎ ግራም ማር ለመሥራት አንዲት ንብ ሁለት ሚሊዮን አበባዎች ላይ አርፋ መቅሰም አለባት፡፡ በንቦች ሕይወት ውስጥ ሌላም አስገራሚ ነገር አለ፡፡ ንግሥቲቱ ማለትም አውራዋ ንብ፣ ጉልበቷ በሚደክምበት ጊዜ ዙፋኗን ለትውልድ ለማስረከብ እንቁላል መጣል ትጀምራለች፡፡ አያሌ የንግሥቲቱ እጮች ቢፈለፈሉም፣ አልጋውን የምትወርሰው በመጀመሪያ የምትበረው አንዷ ንብ ነች፡፡ ይህችም አልጋ ወራሽ ንብ ሕይወት እንደዘራች በቅድሚያ የምትወስደው እርምጃ ያልተፈለፈሉትን የንብ ልዕልቶችን እያደነች መግደል ነው፡፡ በመጨረሻም ብቸኛዋ ነጋሢ መሆኗን ስታረጋግጥ፣ የአመራር ሥልጣኑን "እፎይ"" ብላ ትጨብጣለች፡፡
(ሻለቃ አባይነህ አበራ፣ ጭላሃ ወግ (ትርጉም"፣ 1981)

* * * * * *


አባ ጃሌው!
አባ ጃሌው በሠፈራቸው ከታወቁና አሉ ከሚባሉት ሽማግሌዎች አንዱ ሲሆኑ በጣም የተከበሩ ሰው ናቸው። የሠፈሩ ሰው ማንኛውም ጉዳይ ሲኖረው ሁሌ የሚጠራው እርሳቸውን ሲሆን፣ ለምሳሌ ለሚስት አማጭ ሰው ሲፈለግ እርሳቸውን ለምኖ ከሽማግሌዎቹ መሃል ካስገባ፣ ተጠያቂው እምቢ ብሎ መመለስ በጣም ይከብደዋል። ለዚህም ሁሌ ይቀናቸዋል፣ ጉዳዩም ቶሎ ይፈጸማል። በመሬት ሆነ በገንዘብ የተጣላውን ለመሸምገል ዘወትር ሰው ሁሉ የሚጠራው አባ ጃሌን ነው። ባልና ሚስትም ሲጣሉ ዋና አስታራቂ ከአባ ጃሌው የተሻለ ሌላ የለም፡፡ ስለዚህ አባ ጃሌው የኅብረተሰቡ ዋና ማገርና ምሰሶ ናቸው ቢባል ከሐቁ የራቀ አይሆንም።

አባ ጃሌው እድሜያቸው በትክክል ባይታወቅም፣ አሁን እያረጁ ወደ ዘጠና ዓመት እንደ ተጠጉ ይገመታል። ጥልቅ አስተዋይነታቸውና ብልኅነታቸው የታወቀው ገና ድሮ ሲሆን፣ ያኔ የዓርባ ዓመት እድሜ ያህል እንኳን የነበራቸው አይመስሉም ነበር።

“አባ ጃሌው” ሊባሉ የቻሉት በሠፈሩ ሰው አጠራር እንጂ ትክክለኛው ስማቸውስ አያሌው ነበር። ከሠፈሩ አሮጊቶች አንዷ፣ ፊደል እንኳን ያልቆጠሩት፣ እማሆይ ወለተ-ጽዮን የሚባሉት አንድ ቀን፤ “አባ አያሌው” ለማለት፤ “አባ ጃሌው!” ብለው ሲጠሯቸው፣ ከዚያን ጊዜ ወዲያ ሁሉም ተቀብሎ፣ ስማቸውን ከአባ አያሌው ወደ አባ ጃሌው ለወጠው። በልጅነት የወጣላቸው ትክክለኛው ስማቸው ተረስቷል። ዛሬ ይኸው በሠፈሩ ሁሉ “አባ ጃሌው” በሚል መጠሪያ ስም ብቻ ነው የሚታወቁት።
(በገብረ ኢየሱስ ጎርፉ፤ከመስኮት ድረ ገጽ)

* * * * * *

ገራገር

ያለጐማ በስካር 11 ማይል ያሽከረከሩት አዛውንት
በሳምንቱ መገባደጃ ከኒውዮርክ የተሰራጨው ዜና ለየት ያለ ነው፡፡ የ61 ዓመቱ አዛውንት በስካር መንፈስ ሲያሽከረክሩ ያይዋቸው የትራፊክ ፖሊሶች ቢከታተሏቸውም ሊደርሱባቸው አልቻሉም፡፡ አንድ ጎልማሳ ደግሞ አዛውንቱ የሚያሽከረክሩት መኪና የቀኙ ጎማው የወለቀ መሆኑን ለፖሊስ ይጠቁማል፡፡ ዳኒ ቡሽ የተባሉት አዛውንት ግን በፍጥነት ይሸመጥጡ ስለነበር ፖሊሶች ሊደርሱባቸው አልቻሉም፡፡

በመጨረሻ ላይ ከደቡብ ምዕራብ የችስታር ከተማ 37 ማይል ርቆ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ሲደርሱ ግን አዛውንቱ ቡሽ ምንም እንዳልተፈጠረ ቁጭ ብለው ያገኟቸዋል፡፡ የመንጃ ፈቃዳቸውን ሲጠየቁ ደግሞ ለ33 ዓመት ያልታደሰ መንጃ ፈቃዳቸውን አውጥተው ይሰጧቸዋል፡፡

ዳኒ ቡሽ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ በሁለት ወንጀሎች ክስ ይመሠረትባቸዋል ተብሏል፡፡ ከተፈቀደው በላይ ሦስት ጊዜ እጥፍ ጠጥቶ በማሽከርከርና ለረዥም ዓመት ባልታደሰ መንጃ ፈቃድ በማሽከርከር ናቸው፡፡

* * * * * *

የውስኪ ተረፈ ምርት ለመኪና ነዳጅነት እንደሚያገለግል ጥናት ጠቆመ

ውስኪን ለመኪና ነዳጅነት መጠቀም ምን ይከለክለዋል? የኤደንበርግ ናፕየር ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ከስኮትላንድ ውስኪ ማምረቻ ከሚወጣው ተረፈ ምርት ላይ የነዳጅ ዘይትን በማምረት ይህን ዕውን አድርገውታል፡፡ አዲሱን የውስኪ ተረፈ ምርት ነዳጅ ለመጠቀም አዲስ የመኪና ሞተር መግጠም አያስፈልግም፡፡ እንደ ኮምካስት ዘገባ ከሆነ ነዳጁን ለማንኛውም መኪና መጠቀም ይቻላል፡፡ ተመራማሪዎቹ በእንግሊዝ የጋዝ እስቴሽን ውስጥ አዲሱን ምርት መጠቀም ግን አልቻሉም፡፡

 
 
  HALELUYYAA
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
  namni ilma Waaqayyoo hin qabaanne, jireenyicha hin qabu." 1Yoh 5:12
namni ilma Waaqayyoo hin qabaanne, jireenyicha hin qabu." 1Yoh 5:12

This website was created for free with Own-Free-Website.com. Would you also like to have your own website?
Sign up for free