ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።  
 
  መልስ 01/22/2025 5:02am (UTC)
   
 
ምክንያቱም ሁሉም ኀጢአት ሠርተዋል፤ የእግዚአብሔርም ክብር ጐድሎአቸዋል ሮሜ ፫፥፳፫ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ ይባረክ፤ እርሱ ከታላቅ ምሕረቱ የተነሣ በኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት መነሳት ምክንያት ለሕያው ተስፋ የሚሆን አዲስ ልደት” ሰጥቶናልና ፩ኛ ጴጥሮስ ፩፥፫ በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፉ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና ዮሐንስ ፫፥፲፮ በእውነት መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነውን ? ጥያቄ፤ በእውነት መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነውን ? መልስ፤ ለዚህ ጥያቄ የምንሰጠው መልስ መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት እንደምንመለከተውና ለሕይወታችን ያለውን ጠቀሜታ የሚወሰን ብቻ ሳይሆን በመጨረሻም በኛ ላይ ዘላለማዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል ። መፅሓፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ከሆነ ልንወደው ፣ልናጠናው፣ ልንታዘዘውና ልናምነው ይገባል። መፅሓፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ከሆነ ስለዚህ እሱን መናቅ ማለት እግዚአብሐር ራሱን መናቅ ማለት ይሆናል ። እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስ ሲሰጠን ለኛ ያለውን ፍቅር የገለጸበት መንገድ ነው። “መገለጥ” የሚለው ቃል በቀላሉ ሲተረጎም እግዚአብሔር ምን እንደሚመስልና እኛ ከእርሱ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዴት እንደምንፈጥር ለሰው ልጅ ያስተላለፈበት መንገድ ። በመጽሐፍ ቅዱስ በኩል እግዚአብሔር በመለኮታዊ መገለጡ ባያስታውቀን ኖሮ እነዚህን ነገሮች ማወቅ አንችልም ነበር። ምንም እንኳ እግዚአብሔር ስለራሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ያስታወቀን መገለጥ ቀስ እያለ 1500 አመታት የፈጀ ቢሆንም የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር ሊኖረው ስለሚገባ ግኑኙነት በውስጡ በሙሉ ይዟል ። መጽሐፍቅዱስ በእውነቱ የእግዚአብሔር ቃል ከሆነ እምነትን፣ ሐይማኖታዊ ልምምድንና ሞራልን በተመለከተ ወሳኝ ሥልጣን አለው ማለት ነው ። መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል እንጂ ሌላ መልካም መጽሐፍ መሆኑን እንዴት እናውቃለን ብለን እራሳችንን መጠየቅ አለብን። ከዚህ በፊት ከተጻፉት የሐይማኖት መጻህፍት ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስን ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው ? መጽሐፍ በእውነት የእግዚአብሔር ቃል ስለመሆኑ ማረጋገጫ አለን? መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃልና መለኮታዊ ምንጭ ያለው ለእምነትና ለተግባር ጉዳዮች በቂ መልስ የሚሰጥ ነው ካልን ከላይ የተጠቀሱትን ጥያቄዎች በጥሞና መመርመር ግድ ይለናል ። መጽሐፍቅዱስ እንደሚያውጀው የራሱ የእግዚአብሔር ቃል ስለመሆኑ የቀረበው ሐቅ የሚካድ አይደለም። ይህ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ ባቀረበው ምክር በግልጽ ይታያል ። “… ከሕጻንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፣መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻህፍትን አውቀሃል። የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጐ ስራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጐ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል” (2ኛ ጢሞቲዮስ 3 ፡ 15-17 )። መጽሐፍቅዱስ በእውነት የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ የሚያስረዱ ውስጣዊና ውጫዊ መረጃዎች አሉ። ውስጣዊ መረጃዎቹ በመጽሐፍቅዱስ የሚገኙ ሆነው ስለመለኮታዊ ምንጭነቱ የሚያረጋግጡ ናቸው ። በመጽሐፍቅዱስ በእውነት የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ የሚያረጋግጡት የመጀመሪያዎቹ ውስጣዊ መረጃዎች በመጽሐፉ አንድነት ይታያሉ። ምንም እንኳ መጽሐፍ ቅዱስ የተመሰረተው ከ66 የተለያዩ መጻህፍት ቢሆንም እስካሁን ድረስ አንድ የተዋሐደ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ቅራኔ የሌለበት ነው። መጽሐፍቅዱስ ሲጻፍ በግምት 1500 ዓመታት የፈጀ ሲሆን በሦስት አህጉራት፣ በሦስት የተለያዩ ቋንቋዎች የተለያየ የሕይወት ተሞክሮ ካላቸው 40 ፀሐፊዎች ነው። ይህ አንድነት ከሌሎች መፃህፍት ሁሉ ልዩ ያደርገዋል ። እግዚአብሔር ሰዎችን በአስደናቂ መንገድ አንቀሳቅሶ የራሱን ቃል እንዲመዘግቡ ማድረጉ ለመጽሐፍቅዱስ መለኮታዊ ምንጭነቱ ሌላ ምስክር ነው ። መጽሐፍ ቅዱስ በእውነት የእግዚአብሔር ቃል ለመሆኑ የሚያረጋግጠው ተጨማሪ ውስጣዊ ማስረጃ በገጾቹ ውስጥ የሚታዩት ትንቢቶች ናቸው መጽሐፍ ቅዱስ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዝርዝር ትንቢቶች ተካተውበታል። ስለመጪው የአንዳንድ አገሮች ሁኔታ እስራኤልንም ጨምሮ ተጽፎበታል። ስለ አንዳንድ ከተሞች፣ ስለመጪው የሰው ልጆች ሁኔታ፣ የእስራኤል ብቻ ታዳጊ ሳይሆን ያመኑትም ሁሉ ስለሚታደገው ስለመሲሑም ያብራራል። በሌሎች ሐይማኖታዊ መጻህፍትና በኖስትራዳመስ እንደቀረቡ ትንቢቶች ሳይሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን ሐቀኝነታቸው ለጥርጣሬ ቀርቦ አያውቅም። በብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ብቻ ኢየሱስ ክርስቶስን የሚመለከቱ ከ300 በላይ ትንቢቶች ቀርበዋል ። አስቀድሞ የተተነበየው የት ቦታ እንደሚወለድና ከየትኛው ቤተሰብ እንደሚገኝ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን እንዴት እንደሚሞትና በሦስተኛው ቀን እንደሚናሳ ተነግሮለታል። ከመለኮታዊ ምንጭ ካልሆነ በስተቀር የተፈጸሙትን ትንቢቶች በቀላሉ ለማስረዳት የሚቻል አይደለም። የመጪዎችን ትንቢቶችን በተመለከተ በስፋትም ይሁን በአይነት እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ያቀረበ ሌላ ሐይማኖታዊ መጽሐፍ ቢፈለግ አይገኝም ። መጽሐፍ ቅዱስ ከመለኮታዊ ምንጭ እንደተገኘ የሚያረጋግጠው 3ኛው የውስጣዊ ማስረጃ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ባለው ልዩ ስልጣን ኃይል ይታያል ። ይህ በፊት ከቀረቡት ሁለት ጋር ሲታይ በስሜት ላይ የተመሠረተ ቢመስልም ስለ መጽሐፍ ቅዱስ መለኮታዊ ምንጭነት የሚያቀርበው ምስክርነት ተአማኒነት ያለው ነው ። ከተጻፉት መጽሐፍት ይልቅ መጽሐፍ ቅዱስ የተለየ ሥልጣን አለው ። ይህ ኃይልና ሥልጣን በግልጽ የሚታየው ሉዐላዊ ከሆነው የእግዚአብሔር ቃል የተነሳ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሕይወቶችን በመለወጡ ነው ። የዕፅ ሱሰኞች በእርሱ ተለውጠዋል ፣ ግብረ ሰዶማዊያን ነጻ ወጥተዋል ፣ የተናቁና ሰነፎች ተለውጠዋል ፣ የወጣላቸው ወንጀለኞች ተሻሽለዋል ፣ ኃጢያተኞች ተገሥፀዋል ፣ እርሱን በማንበብ ጥላቻ ወደ ፍቅር ተቀይሯል ። መጽሐፍ ቅዱስ በውስጡ ጉልበትና ኃይል አለው። ይህም የሆነው ያለምክንያት አይደለም በእውነት የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በእውነቱ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን የሚያሳዩ ሌሎች ውጫዊ መረጃዎች አሉ ። ከነዚህም አንዱ መረጃዎች በታሪኩ የተመሰረተ መሆኑ ነው ። መጽሐፍ ቅዱስ ታሪካዊ ሁኔታዎችን ስለሚዘግብ ሐቀኝነቱና ትክክለኛነቱ እንደሌላው የታሪክ መዝገብ ሊመዘን ይችላል ። የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪካዊዘገባዎች በመሬት ቁፋሮ በሚገኙ መረጃዎችና ሌሎች ጽሑፎች ትክክለኛነታቸው ተረጋግጧል። የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውነታ ያረጋገጡት በመሬት ቁፋሮ የተገኙ መረጃዎችና ብራናዎች ከጥንት ጀምሮ ከነበሩ መጽሐፍት ውስጥ ታሪካዊ ሁኔታዎችን የዘገበ መሆኑን መስክረውለታል ። መጽሐፍ ቅዱስ በታሪክ ሊረጋገጡ የሚችሉ ትክክለኛና ሐቀኛ ሁኔታዎችን መዝግቦ መያዙ ሃይማኖታዊ ርዕሶችንነ መመሪያዎችን በተመለከተ የመዘገባቸው ጉዳዮች ሐቀኛ መሆናቸውን ከማመልከቱም በላይ ከእግዚአብሔር ከራሱ የተገኘ ቃል መሆኑን ያፀኑለታል ። መጽሐፍ ቅዱስ በእውነት የእግዚአብሔር ቃል ለመሆኑ ሌላው ውጫዊ መረጃ የፀሐፊዎቹ ሐቀኝነት ነው ። ከዚህ በፊት እንደተጠቀሰው እግዚአብሔር ከተለያየ የሕይወት ዘርፍ የተገኙትን ሰዎች በመጠቀም ቃሉን ለኛ እንዲጽፉ አድርጓል ። የነዚህ ሰዎች ሕይወት ስንመረምር ሐቀኛና ታማኝ መሆናቸውን የሚያስተባብል ምክንያት አልተገኘም ። ህይወታቸውን ስንፈትሸውና ለሚያምኑበት ነገር ብዙ ግዜ አሰቃቂ ሞት ለመሞት ፍቃደኛ መሆናቸውን ስናይ እነዚህ ተራና ቅን ሰዎች እግዚአብሔር እንደተናገራቸው እንደሚያምኑ ግልጽ ይሆንልናል አዲስ ኪዳንን የጻፉት ሰዎች ሌሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ አማኞች የመልዕክቱን እውነተኛነት አውቀዋል ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ ከመቃብር ከተነሳ በኋላ አይተውታል ከእርሱም ጋር የተወሰነም ቆይታ አድርገዋል ። ከሞት የተነሳው ኢየሱስ ክርስቶስ ለማየት ከባድ ተፅዕኖ አሳድሮባቸዋል ። በፍርሀት ተሸማቀው ከተደበቁበት ወጥተው እግዚአብሔር ለገለጠላቸው መልዕክት ለመሞት ፍቃደኛ ሆነዋል ህይወታቸውና ሞታቸው መጽሐፍ ቅዱስ በእውነት የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን አስመስክሯል ። መጽሐፍ ቅዱስ በእውነት የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ ለመጨረሻ የምናቀርበው ውጫዊ መረጃ የመጽሐፍ ቅዱስ በዘመናት ውስጥ አለመጐዳት ነው ። (ወይም አለመጥፋት ነው)። ከጠቀሜታው አንጻርና የራሱ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ማወጁ መጽሐፍ ቅዱስ በታሪክ ከታዩት መጽሐፍት ውስጥ በይበልጥ እንዲጠፋ ጐጂ ጥቃቶችና ሙከራዎች ተሰንዝረውበታል ። እንደ ዲዮቅሊጣን ከመሳሰሉ የጥንት የሮማ ነገሥታት ጀምሮ እስከ ኮሚኒስት አምባገነኖችና በዘመናችን ከሚገኙ የእግዚአብሔርን መኖር ከማያምኑና የሰው አዕምሮ የእግዚአብሔርን መኖር ሊያውቅ አይችልም ብለው ከሚገምቱ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ተቋቁሞ አጥቂዎቹን አሸንፎ አሁን በዓለም ከሚታተሙት መጽሐፍት ቀዳሚነትን ይዟል ። በዘመናት መካከል ተጠራጣሪዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንደ አፈ ታሪክ ሲመለከቱት ቆይተዋል ። የመሬት ቁፋሮ ሳይንስ ግን ታሪካዊነቱን አረጋግጦለታል ። ባላንጣዎቹ ትምህርቱን ኋላቀርና ግዜው ያለፈበት ብለው አውግዘውታል ። ነገር ግን የመጽሐፍ ቅዱስ የሞራልና የሕግ አመለካከቱና ትምህርቱ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ማህበረሰቦችና ባህሎች በጐ ተፅዕኖውን አሳድሯል ። አሁንም ቢሆን በሳይንስ ፣ በሳይኮሎጂና በፖለቲካ እንቅስቃሴዎች እንደተወረፈ ነው። ይሁን እንጂ በመጀመሪያ ሲጻፍ እንደነበረው አሁንም እውነተኛና ተፈላጊ ነው ። ባለፉት 2000 ዓመታት የብዙ ለቁጥር የሚታክቱ ሰዎችና ባህሎችን የለወጠ መጽሐፍ ነው ። ጠላቶች የቱን ያህል ለማጥቃት ፣ ለማጥፋትና ዋጋ ለማሳጣት ጥረት ቢያደርጉም ከጥቃቱም በኋላ ቢሆን እንደቀድሞው ጉልበታም ኃይለኛና ተፈላጊ ነው ። ሊበርዙት ፣ ሊያጠቁትና ሊያወድሙት ጥረት ቢያደርጉም ትክክለኛነቱ እንደተጠበቀ ይቆያል ። ይህም በግልጽ የሚያሳየው መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑንና በመለኮታዊ ኃይሉ ጥበቃ እንደሚያደርግለት ነው ። አንድ ሊያስደንቀን የማይገባ ነገር አለ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያህል ጥቃት ቢደርስበትም ሳይለወጥና ጉዳቱ ምንም ንክች ሳያደርገው ቀርቷል ። ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ኢየሱስ እንደዚህ ብሏል “ ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም”። ማስረጃዎቹን ካየን በኋላ ያለመጠራጠር አዎ መጽሐፍ ቅዱስ በእውነት የእግዚአብሔር ቃል ነው ማለት እንችላለን ። ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ በእውነት መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነውን ? በእምነት፣ በጸጋ ድናችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ በሥራ አይደለም ኤፌሶን ፪፥፰-፱ ‘ኢየሱስ ጌታ ነው’ ብለህ በአፍህ ብትስክር፣ እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሳው በልብህ ብታምን፣ ትድናለህ ሮሜ ፲፥፱ ነግር ግን ገና ኀጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞተ፤ ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያሳያል ሮሜ ፭፥፰
 
 
  HALELUYYAA
 
 
 
 
 
 
 
 
 
  namni ilma Waaqayyoo hin qabaanne, jireenyicha hin qabu." 1Yoh 5:12
namni ilma Waaqayyoo hin qabaanne, jireenyicha hin qabu." 1Yoh 5:12

This website was created for free with Own-Free-Website.com. Would you also like to have your own website?
Sign up for free